Announcement ክህሎት ልማት እሳቤዎች ለቀጣሪ ድርጅቶች በሚል በኮሌጁ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ::

ክህሎት ልማት እሳቤዎች ለቀጣሪ ድርጅቶች በሚል በኮሌጁ የውይይት መድረክ ተካሂዷል ::

02nd July, 2025

ሰኔ :- 20/2017 ዓ.ም ቂ.ማ.ኮ


በቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በስልጠናናአካዳሚክ ጉዳዮች የስራ ክፍል አዘጋጅነት ለቀጣሪ ድርጅቶች የትብብር ስልጠና የሚሰጡ ኢንደስትሪዎች ባለ ድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል :: በውይይቱ ክህሎት መር የስራና ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ ያስችል ዘንድ ክፍተቶችን ለመሙላትና የተጀመሩትን ለማስቀጠል በየደረጃው የሚገኙ የቀጣሪ ድርጅቶች የትብብር ስልጠና የሚሰጡ ኢንደስትሪዎች እና ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የስራና ክህሎት ዘርፉ አዲስ እሳቤዎች የክህሎት መር ልማት፣ በተቋም ግንባታ፣ ምቹ የስራ ከባቢ ከመፍጠር አንፃር፣ የስራ ዕድል ፈጠራና የስራ ስምሪትን ፣ ሰላማዊ የኢንዱስትሪ ዞን ከመፍጠር አኳያ አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ አጠቃላይ ውይይት አድርገዋል:: በውይይቱ ማጠቃለያ የኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ክ ዲን እና የቴክኖሎጂ ልማት ኢንደስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዋና ዲን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ በመስጠት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል ::

.

Copyright © All rights reserved.

Created with